በመጪው  ከጥር እስከ መጋቢት  ወራት የአፍሪካ ቀንድ   ከባድ ዝናብ  ያስተናግዳል

344

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21/2016 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ  ከጥር እስከ መጋቢት ከባድ ዝናብ  እንደሚጥል ኢጋድ አስጠነቀቀ።

 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት  ባለስልጣን የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል እንዳስታወቀው፤  በጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ከጥር እስከ መጋቢት 2024 ወራት  አብዛኛው የአፍሪካ ቀንድ  ከባድ ዝናብ እንደሚጥል ተንብይዋል።

በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ የኤልኒኖ ተጽኖ ምክንያት መሆኑንም ማዕከሉ አስታውቋል።

መቀመጫውን በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ያደረገው ማዕከሉ በትንበያው እንዳስታወቀው፤በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ለሚጥለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የሁኑ እርጥበታማ የአየር ሁኔታዎች በደቡባዊ እና ኢኳቶሪያል አካባቢ በሚገኙ የቀጠናው ክፍሎች ላይ ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ እንደሚጠበቁ ማዕከሉ ገልጿል።

ከጥር እስከ መጋቢት ከባድ ዝናብ ከሚያስተናጉዱት ሀገራት መካከልም ታንዛኒያ፣ብሩንዲ፣ኬንያ፣ደቡብ ኡጋንዳ እንዲሁም ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ እንደሚገኙበት ማዕከሉ አስታውቋል።

ማዕከሉ ጨምሮ እንዳስታወቀው፤ በዚህ ወቅት ከመደበኛው ሁኔታ በላይ ደረቃማ ሁኔታ  እንደሚኖር አመልክቷል።

ደረቅ የሚሆኑት አካባቢዎችም በማዕከላዊ ኬንያ፣ በሰሜን እና በምዕራብ ታንዛኒያ በሚገኙ ጥቂት ቦታዎች ላይ ነው ብሏል።

የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በአጠቃላይ ከጥቅምት እስከ ታህሣሥ ባለው ጊዜ በገጠማቸው የዝናብ እጥረት ድርቅ እንደነበረ ያስታወሰው ማዕከሉ፤ ይህም የአየር ንብረት ለውጥ የአየር ሁኔታውን እየቀየረ መሆኑን ገልጿል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል በአካባቢው ከሚጠበቀው ከባድ ዝናብ በተጨማሪ፣ የሙቀት መጠኑ ከመደበኛው በላይ እንደሚሆንም አመልክቷል።

በዚህ ወቅት በመኪሰተው ሙቀት የከፋ ጉዳት የሚደርስባቸው ቦታዎች የሰሜን ኬንያ፣ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያን የተለያዩ ክፍሎች እንደሚያጠቃልል ያስታወቀው ማዕከሉ፤ በዚህ ወቅት የሚከሰተው የሙቀት መጠን ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልስየስ ሊጨምር እንደሚችልም ተንብይዯል።

የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሊጠናቀቅ ሰዓታት በቀሩት የፈረንጆቹ ዓመት ፈጣን የአየር ሁኔታ ለውጦች ማገጠሙን ያመለከተው ማዕከሉ፤ በጥቅምት ወር በአካባቢው የጣለው የኤልኒኖ ዝናብ በጎርጎርሲያኑ አቆጣጠር ከጥር 2024 እስከ መጋቢት ባለው ጊዜ ከፍተኛ ዝናብ አስከትሎ ይከሰታል ብሏል።

በቀጠናው የተራዘመ ድርቅ አለያም   የጎርፍ   አደጋዎች  በሰዎች  ላይ ጉዳት  ማድረሱን ዥንዋ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም