የሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 21/20216 (ኢዜአ)፦የሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።