ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው

ዋግ ኽምራ ፤ ታህሳስ 21/2016 (ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።  

ውይይቱም በሰላም፤ በልማትና በመልካም አስተዳደር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።  


 

በመድረኩ ላይም በሃገር መከላከያ ሰራዊት የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ፣ የተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ዳይሬክተር ብርጋዴል ጄኔራል ደርቤ መኩሪያ፣ ጨምሮ ሌሎች  የክልልና የብሄረሰብ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም