ቀጥታ፡

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አየር ማረፊያ ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 20/2016(ኢዜአ)፦ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከተለያዩ የፌደራልና የክልሉ መንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን የኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አየር ማረፊያ ግንባታ ጎብኝተዋል።


 

ፕሬዝዳንቱ ከፌደራልና ከክልሉ መንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በጎዴይ ከተማ የኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አየር ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት የስራ ሂደትን መመልከታቸውን የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

በጉብኝቱ ላይ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና  የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም