አምባሳደር ተፈራ ደርበው በቻይና ሚዲያ ሽልማት ተሰጣቸው - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ተፈራ ደርበው በቻይና ሚዲያ ሽልማት ተሰጣቸው
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 20/2016 (ኢዜአ)፦ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ' ዘ ኒውስ ፐርሰን ኦፍ ዘ ይር 2023 ' በሚል በቻይና “ሆም ኤንድ አብሮድ ኒውስ ፕሬስ” ሚዲያ ተሸለሙ።
አምባሳደሩ ሽልማቱን ያገኙት ሆም ኤንድ አብሮድ ኒውስ ፕሬስ 22ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ ነው፡፡
በሽልማቱ ስነ-ስርዓቱ ላይ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ለሽልማቱ በመብቃታቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ሽልማቱን ለሰጣቸው ሚዲያም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አምባሳደር ተፈራ ደርበው ሚዲያ ለአለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የተናገሩ ሲሆን በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡
ቻይናና ኢትዮጵያ ታሪካዊና ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ጥልቅ ግንኙነት በመመስረት ባለፉት አምሳ አመታት በወዳጅነት መዝለቃቸውንም ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባለፈው ጥቅምት ወር ቻይናን በጎበኙበት ወቅት የሁለቱ ሀገሮች ትብብር በተለያዩ ዘርፎች የበለጠ ያደገበት መሆኑንም አምባሳደሩ በሽልማቱ ወቅት አንስተዋል፡፡
ሆም ኤንድ አብሮድ ኒውስ ፕሬስ በቻይና መሰረቱን አድርጎ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀስ የሚዲያ ተቋም ሲሆን በአሜሪካ በካናዳ በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝ እና በሌሎች ሀገራት ቅርንጫፎች አሉት፡፡