ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ 528 የመንግስት አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 19/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ በተለያዩ ተቋማት 528 የመንግስት አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ መሆናቸው ተገለፀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሰራተኞች በአይ ሲ ቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የቀጣይ ስራዎች ላይ ምክክር እያደረጉ ነው።

ከእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ 321ዱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባለማው የኦንላይን አገልግሎት መስጫ ስርዓት ላይ የሚሰጡ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማፋጠን የአይ ሲቲ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዝርጋታና የማሻሻያ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።


 

ዜጎች ባሉበት ሆነው የመንግስት አገልግሎቶችን በቀጥታ እንዲያገኙ ለማድረግ አመርቂ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸውም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ስለመሆናቸው አብራርተዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስራን የሚያሳልጡ ሀገራዊ የቢዝንስ ፖርታል ማስፋፊያ ስራ፣ የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ፣ የኢትራንዛክሽን ማስፈፀሚያ ደንብ፣ የኤሌክትሮኒክ መንግስት ስትራቴጂ ስራዎች ላይ ሰፋፊ ስራዎች ስለመሰራታቸው ማንሳታቸውን ከኢኖቬሽን ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም