ህንድ ለጂኦ ኢንተለጀንስ አገልግሎት የሚውሉ 50 ሳተላይቶችን ልታመጥቅ ነው

350

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 19/2016 (ኢዜአ)፡- ህንድ ለጂኦ ኢንተለጀንስ አገልግሎት የሚሰጡ 50 ሳተላይቶችን  ወደ ህዋ የማመንጠቅ ዕቅድ እንዳላት ተገለጸ።

የአገሪቱን የጠፈር ምርምር ድርጅት ዋና ኃላፊ ኤስ ሶማታንን  ጠቅሶ የዘሂንዱ ድረገጽ እንደዘገበው ሳተላይቶቹ በሚቀጥሉት አምስት አምታት ወደ ህዋ የሚመነጠቁ ናቸው።

እስካሁን የአብዛኛዎቹ ሳተላይት ንድፍ  እና ቀመር መጠናቀቃቸውን ኃላፊው ጠቁመው  ሳተላይቶቹ በጠፈር ላይ  በተለያዩ ምህዋሮች እየተሽከረከሩ ከሺህ ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ እንቅስቃሴዎችን ከመከታተል ባለፈም የምስል መረጃ  የመላክ አቅም ያላቸው እንደሆኑም አብራርተዋል።

ህንድን ከአለም ጠንካራ አገሮች ተርታ  ለማሰልፍ ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል የመረጃ ሳተላይት ሰርቶ የማመንጠቅ ስራ አንዱና  ዋነኛው መሆኑን የጠፈር ምርምር ተቋም ሊቀመንበር ኤስ ሶማታን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት አገሪቱ የምትጠቀምባቸው የሳተላይት ቴክኖሎጂዎች አቅም ውስንነት ያለባቸው መሆኑን ጠቁመው ወደፊት አገሪቷ የምታምጥቃቸው የሳተላይት አይነቶች በብቃት ከአሁኖቹ በአስር እጥፍ የላቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ህንድ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ የሳተላይት ቴክኖሎጂዎችን አምርቶ ለማመንጠቅ  መዘጋጀቷንም መረጃው አስታውሷል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም