ቀጥታ፡

የቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 19/2016 (ኢዜአ)፦ የቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ለብዙሃን መገናኛ በላከው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የተከበረው የቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም መጠናቀቁን ገልጿል።

በዓሉ በሰላም አንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለሀይማኖት አባቶች፣ እና ለአካባቢው ኅብረተሰብ እንዲሁም ለበዓሉ ከፍተኛ የደኅንነት ጥበቃ ላደረጉ የፀጥታ አካላት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

ከበዓሉ ታዳሚዎች የሞባይል እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ሰርቀው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች በፈፀሙት ወንጀል ጥፈተኛ ሆነው በመገኘታቸው በተቋቋው ጊዜያዊ ችሎት (RTD) ቀርበው ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ከሦስት ወር በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን የጋራ ግብረኃይሉ በመግላጫው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም