የኡጋንዳ መከላከያ ኤዲኤፍ የተሰኘው የሽብር ቡድን መሪ መገደሉን ገለጸ

299

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 19/2016 (ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 19/2016 (ኢዜአ)፦ የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት በምዕራባዊ ኡጋንዳ የሽብር ጥቃቶችን እየፈጸመ ነው ያለውንና የተባበሩት ዴሞክራሲያዊ ግንባር በሚል የሚጠራውን ቡድን መሪ መግደሉን አስታወቀ።

የኡጋንዳ ህዝቦች መከላከያ ሠራዊት እንዳስታወቀው በዚህ ወር በሀገሪቱ ተከስቶ ለነበረውና 13 ሰዎች ለሞቱበት የሽብር ተግባር ተጠያቂ የነበረው የኤዲኤፍ መሪ መከላከያ ሠራዊቱ በወሰደው ወታደራዊ ዘመቻ ተገድሏል።

የሰራዊቱ ምክትል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ዴዎ አኪኪ እንደተናገሩት የሽብር ቡድኑ መሪ ሙሳ ካሙሲ እርምጃ ተወስዶበታል።

አሸባሪው ታህሳስ 8 እና 16 በኪባሌ ብሔራዊ ፓርክ በተፈጸመው ጥቃት ዋነኛ መሪ የነበረ ሲሆን በዚህም የሰዎች  ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም የኡጋንዳ ህዝቦች መከላከያ ሠራዊት ቀጣናውን ከአሻባሪዎች ነጻ የማድረግና ወደ ቀደመ ሰላሙ የመመለስ ተግባር በተጠናከረ ሁኔታ እያከናወነ እንደሚገኝ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

አሸባሪ ቡድን ከቅርብ አመታት ወዲህ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቱሪስቶችን ጨምሮ በንጹሃን ላይ የሽብር ተግባር በመፈጸም ተጠያቂ የተደረገ ቡድን መሆኑን አናዶሉ ዘግቧል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም