ቻይና ለአየር ንብረት  ትንበያ የሚያገለግሉ አራት ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ላከች

294

አዲስ አበባ ፤ ታህሣሥ 17/2016 (ኢዜአ)፦ ቻይና ለአየር ንብረት  ትንበያ የሚረዱ አራት አዲስ ሳተላይቶችን በያዝነው ሳምንት ወደ ህዋ መላኳን አናዶሉ አስነብባል።

ከሀገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ጂውኩዋን ከተባለው የጠፈር ማምጠቂያ ማእከል የተደረገው ሳተላይቶቹን የማምጠቅ ሂደት ስኬታማ እንደነበርና በእለቱም ሁዋይ ዡ 1ኤ የተሰኘችው ሮኬት እንደመጠቀች ይፋ ተደርጓል።

ሁዋይ ዡ 1ኤ የተባለችው ሮኬት ለ24ኛ ጊዜ መምጠቋን ተከትሎ ቻይና ለንግድ፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚውሉ ተጨማሪ አራት ሳተላይቶችን ከቀናት በፊት እንዳመጠቀች ተገልጿል።

ወደ ህዋ የተላኩት ሳተላይቶች ወደታቀደላቸው ምህዋር መድረሳቸውና የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን እንደሚልኩም በመረጃው ተመላክቷል።

ቻይና ማክሰኞ ወደ ህዋ ከላከቻቸው አምስት ሳተላይቶች መካከል ሶስቱ ሺያን -24ሲ የሚባሉና የስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ነክ ለሆኑ ምርምሮች የሚያገለግሉ እንደሆነም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም