ቀጥታ፡

በጋምቤላ ከተማ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እጽ ሲያለማ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ጋምቤላ ፤ታህሳስ  17/2026 (ኢዜአ) ፦ በጋምቤላ ከተማ በመኖሪያ ጊቢው አካባቢ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እጽ ሲያለማ የተገኘ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የጋምቤላ ከልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፖል ጆክ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለፁት በመኖሪያ ግቢው አካባቢ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ሲያለማ የተገኘ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር  የዋለው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል መሆኑን ገልፀዋል። 

ግለሰቡ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የማጣራት ስራው እንደተጠናቀቀ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚተላለፍ ምክትል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል። 

ኮሚሽነሩ አክለውም በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ሁኔታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ የቁጥጥርና የክትትል ስራ ይጠናከራል ብለዋል። 

በቅርቡ  80 ኪሎ ግራም የሚመዝን የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ ከመሐል አገር ተጓጉዞ ጋምቤላ ከተማ ሲደርስ መያዙን  ይታወሳል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም