ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፈረንጆቹን ገና ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፈረንጆቹን ገና ለሚያከብሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የሚከበረውን የፈረንጆቹን ገና ወይም ክሪስማስ በዓል በማስመልከት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የፈረንጆቹን ገና የምታከብሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እንኳን አደረሳችሁ ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉን ለምታከብሩ ለመላው የአለም ህዝቦች እንዲሁም ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም