ቀጥታ፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በእሲያ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አደረገ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 14/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በእሲያ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የበይነ መረብ ስብሰባ አደረገ፡፡


 

ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያውያን እና ከትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባ ተሳትፎ እና ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ድጋፎች በውይይቱ ተነስቷል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሚሽኑ አባላት ኮሚሽኑንና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፣ ለኢትዮጵያ ስላለው ፋይዳ፣ በኮሚሽኑ ስለተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እና ኮሚሽኑ ስለሚገዛባቸው የህግ ማዕቀፎች ላይ መግለጫዎችን አቅርበዋል፡፡

ገለፃውን ተከትሎ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው መንገዶች ምክረ-ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

ኮሚሽኑ በአሰራር ሂደቱ ላይ ሊያስብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተነስተው አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ ሀሳቦች መነሳታቸውን ከምክክር ኮሚሽኑ ማህበራዊ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም