ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እምቅ የቱሪዝም ኃብት ያላትና ልትጎበኝ የሚገባት ሀገር እንደሆነች መገንዘብ ችያለው - ማርከስ ሳሙኤልሰን  

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13/2016 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ  እምቅ የቱሪዝም ኃብት ያላትና  ልትጎበኝ የሚገባት ሀገር እንደሆነች መገንዘብ ችያለሁ ሲል ትውልደ ኢትዮጵያዊ የምግብ ዝግጅት ሙያተኛው ማርከስ ሳሙኤልሰን ተናገረ፡፡ 
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር የኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅ መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊ  የምግብ ዝግጅት ሙያተኛው ማርከስ ሳሙኤልሰን ኢትዮጵያ ብዙ ሊለማ የሚችል የተፈጥሮ ፀጋዎች እንዳሏትና የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅ በጣም እንዳስደመመው ተናግሯል፡፡

 ኢትዮጵያ በጣም ቆንጆ አገር እንደሆነች መገንዘብ ችያለው ሁሉም ነገር በጣም አስደማሚ ነው ሲልም አንስቷል፡፡

ኢትዮጵያ እምቅ የቱሪዝም ኃብት የተለያየ ባህል እና ቋንቋ ያላት አገር በመሆኗ ልትጎበኝ የሚገባት ሀገር ናት ያለው ማርከስ ሳሙኤልሰን እድገቷና ተፈጥሮአዊ ፀጋዋ እንዳስደመሙት አንስቷል፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በውጭ ሀገራት የተወለዱ ሁለተኛው ትውልድ የዳያስፖራ አባላት ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ባቀረቡት ጥሪ መሰረትም በቀጣይ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ ተናግሯል፡፡

ብዙ ሊጎበኙ የሚችሉ ነገሮች ያላት ሀገር በመሆኗ የኢትዮጵያ የዲያስፖራ አባላትም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው መጥተው እንዲጎበኙ መልክት አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም