ቀጥታ፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከጅቡቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዲሌይታ መሀመድ ዲሌይታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 13/2016 (ኢዜአ)፡- ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በጅቡቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዲሌይታ መሀመድ ዲሌይታ የተመራውን የልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።


 

በሁለቱ ወዳጅ አገሮች ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ዙርያ መወያየታቸውን የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ፕሬዚዳንቷ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖው ለ10 ዓመታት ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡  ዲሌይታ በኢትዮጵያ አምባሳደር እንደነበሩም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም