ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ድጋፍ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 12/2016 (ኢዜአ)፡- በቴል-አቪቭ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተካሄደ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ላይ የሚሲዮኑ ባልደረቦች ለግድቡ ግንባታ የሚውል ከ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ የህዳሴው ግድብ ከተጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ ስኬት የገንዘብ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
የሚሲዮኑ ባልደረቦች ለግድቡ ግንባታ በዲፕሎማሲው መስክ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለሌላው ተምሳሌት መሆን እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
አገራዊ ደህንነት እና ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስከበር እንዲቻል በፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ዲጅታል ንቅናቄ ስራዎች ሁሉም የኤምባሲው ሰራተኞች በንቃት መሳተፍ አስፈላጊነት ላይ በስፋት ውይይት መደረጉን በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።