ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም 62 በመቶ መድረሱን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም 62 በመቶ መድረሱን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 12/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም 62 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ዛሬ ገምግመዋል፡፡
ከ2013 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ12ኛ ጊዜ ባካሄድኩት የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግምገማ በለወጥነው የፕሮጀክት አስተዳደር እና ክትትል ስርዓት የተነሳ የአጠቃላይ ግንባታው ሂደት 62 በመቶ ላይ መድረሱን በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነታቸው አንደኛ እና ሶስተኛ የሆኑትን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እና የኮይሻ ግድቦች ባለቤት በመሆናችን የንፁህ የኃይል ማመንጨት ስራችንን እና ጥረታችንን አቻ የሌለው ያደርገዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በቅርብ ርቀት በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘውን የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅን በምንመርቅበት በአሁኑ ወቅት የኮይሻ ግድብ ለአካባቢው የቱሪዝም ዕድል ተጨማሪ አስተዋፅኦ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡