ኢትዮጵያ ወደ አለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የሚያስችላትን ቅድመ ሁኔታ ፈጥና ለማጠናቀቅ እየሰራች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ወደ አለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የሚያስችላትን ቅድመ ሁኔታ ፈጥና ለማጠናቀቅ እየሰራች ነው
አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 11/2016(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ ወደ አለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የሚያስችላትን ቅድመ ሁኔታ ፈጥና ለማጠናቀቅ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ።
አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅትን መቀላቀል ሂደትን በተመለከተ ከድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዢያንግቺን ዣንግ ጋር በጄኔቫ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
ኢትዮጵያ ወደ አለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የሚያስችላትን ቅድመ ሁኔታ ፈጠና ለማጠናቀቅ እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ንግድ ድርጅቱ ለመቀላቀል ያሉ ውስብስብ ሄደቶችን ለማለፍ በቁርጠኘነት እየሰራች መሆኑንም አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል፡፡
የአለም የንግድ ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ዢያንግቺን ዣንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የንግድ ድርጅቱን ለመቀላቀል የሚያስችለውን ሂደት ለማፋጠን የሄደችበትን ፍጥነትና ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡
ኢትየጵያ በንግድ ድርጅቱ ቅድሚያ የሚሰጣት ሀገር መሆኗንና የአለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል ያለውን ውስብስብ ሂደት ለማለፍ ለምታደርገው ጥረት እውቅና እንሰጣለን ብለዋል፡፡
አምባሳዳር ምስጋኑ ከድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋር ያደረጉት ውይይት ኢትየጵያ የንግድ ድርጅቱን ለመቀላቀል የምታከናውነው ተግባር በመልካም እንዲታይ ያስቻለ መሆኑንም በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡