በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የተመራ ልዑክ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የሚቲዎሮሎጂ ማእከልን ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የተመራ ልዑክ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የሚቲዎሮሎጂ ማእከልን ጎበኘ
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 11/2016(ኢዜአ)፡- በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን የተባበሩት የአረብ ኤሚሬትስ የሚቲዎሮሎጂ ማእከልን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱም የማዕከሉን የትንበያ፣ የጥናትና ምርምር፣ የደመና ማበልፀግ፣ ለአሀዛዊ ትንበያ የሚውል ሱፐር ኮምፒዩተር፣ ዳታ ሴንተር እንዲሁም 7D ሳይንስ ዱምን መጎብኘታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ከዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ፕሬዝዳንት እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚቲዎሮሎጂ ማእከል ዋና ዳይሬክተር አብደላ አልመንዱስ (ዶ/ር) ጋር በአየር ሁኔታ መከታታያ ራዳር፣ በደመና ማበልፀግ በአይሲቲ መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በሰው ኃይል ልማት ላይ እና በአቅም ግንባታ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢስቲትዩት አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።