በጅቡቲ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የተመራው ልዑክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
በጅቡቲ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የተመራው ልዑክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጎበኘ
አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 11/2016 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ድልኤታ መሀመድ ድልኤታ የተመራው ልዑክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጎብኝቷል፡፡
ልዑኩ በሙዚየሙ የሚገኙ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ የሰው ዘር አመጣጥ ላይ ያሉ የአንትሮፖሎጂ ግኝቶችን፣ የኢትዮጵያን ሥልጣኔ የሚያሳዩ አርኪዎሎጂዎችንና ታሪካዊ ቅርሶችን ጎብኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በዓለም ደረጃ የተገኙ አርኪዎሎጂዎችና ታሪካዊ ቅርሶችን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡
የጅቡቲ ሞክር ቤት ፕሬዝዳንት ድልኤታ መሀመድ ድልኤታ በሙዚየሙ ባደረጉት ጉብኝት ደስተኛ መሆናቸውን መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።