ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኩዌት ኤሚር ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኩዌት ኤሚር ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2016(ኢዜአ) ፦ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኩዌት ኤሚር ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ህልፈተ ህይወት አስመልክቶ ለኤሚር ሼኽ መሻል አል አሕማድ አል ሳባህ፣ ለንጉሣዊ ቤተሰብና ለአገሪቱ ሕዝብ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ስም ሃዘናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያና ኩዌት ግንኙነት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አንስቶ ጠንክሮ የቆየ ሲሆን በኩዌት ፈንድ አማካኝነት ለኢትዮጵያ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
በኢራቅና ኩዌት ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያ የኩዌትን መወረር በይፋ መቃወሟ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንቷ በኩዌት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መጎብኘታቸውንም ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።