ቀጥታ፡

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የትብብር ስራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆኗነ ገለጸች

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2016 (ኢዜአ)፡- ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የትብብር ስራዎችን ለማከናወን መዘጋጀቷ ተገለጸ።

የቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ  አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ውይይት ተካሂዷል።


 

በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢንጅነር) ስለ ኢንስቲትዩቱ ሥራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ 

ሁለቱ ተቋማት በቴክኖሎጂ ፣በአቅም ግንባታ፣ በምርምር እና ልማት ስራዎች አብረው ለመስራት እንደሚችሉ በውይይቱ ተመላክቷል። 

የቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራር የሆኑት ሬን ሆንግቦ ተቋማቸው ለኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑ መግለጻቸውን ከኢንስቲቲዩቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም