ቀጥታ፡

የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2016 (ኢዜአ)፦ የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ እንዳስታወቀው የህዳር ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 28 ነጥብ 3 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ሸቀጦች 30 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች 26 በመቶ በመሆን መመዝገቡ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በጥቅምት ወር ከነበረበት 29 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 28 ነጥብ 3 በመቶ መቀነሱን መረጃው ያሳያል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም