በጅቡቲ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ዲሌታ መሀመድ የተመራ ልኡክ አዲስ አበባ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በጅቡቲ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ዲሌታ መሀመድ የተመራ ልኡክ አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ ታህሳስ 9/2016 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ዲሌታ መሀመድ የተመራ ልኡክ አዲስ አበባ ገብቷል።
ልኡኩ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አቀባበል አድርገውለታል።
አፈ ጉባኤው ዲሌታ መሀመድን ጨምሮ የኢትዮ-ጅቡቲ የወዳጅነት ቡድን ሊቀ መንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የጅቡቲ ፓርላማ አባላት በልኡኩ የተካተቱ መሆኑ ታውቋል።
ልኡኩ በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታም የሁለቱን አገራት ፓርላማዎች ወዳጅነት በሚያጠናክሩ ስራዎች ዙሪያ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
እንዲሁም አፈ ጉባኤው ለፓርላማ አባላት ንግግር እንደሚያደርጉ እና የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።