ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ተርክዬ በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2016 (ኢዜአ)፡- የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሌንሳ መኮንን በኢትዮጵያ የተርክዬ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር  ሁለቱ ሃገራት በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ሁኔታ  ላይ ውይይት አድርገዋል።

በቱሪዝም ዘርፍ በተለይም በማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ላይ ተርክዬ ያላትን ልምድ ለቱሪዝም ሚኒስቴር ማካፈል በምትችልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስታውቀዋል፡፡


 

ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ከሚያስተናግዱ የተርክዬ ከተሞች አንዷ የሆነችው ካፓዶኪያ ከተማ እንደ ድሬዳዋ ካሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ጋር ግንኙነት መፍጠር በሚችሉበት መንገድ ላይም መግባባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን በተርክዬ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ለማመቻቸት አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ አምባሳደሩ መግለፃቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም