ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የ450 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ከ ሲቲ ባንክ ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የ450 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ከሲቲ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።

ገንዘቡ ለአምስት አዳዲስ አውሮፕላኖች መግዣ የሚውል መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ከሚገዙት አውሮፕላኖች ውስጥ ሶስቱ ቦይንግ 737 -8 እና ሁለት ቦይንግ 777 ኤፍ የጭነት አውሮፕላኖች ናቸው።

የአምስቱ አውሮፕላኖች ግዢ የአየር መንገዱን የአውሮፕላን ቁጥር ወደ 150 እንደሚያሳድገውም በመረጃው ተመላክቷል።

የብድር ሥምምነቱ አየር መንገዱ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋት እና በዘርፉ ለመድረስ ያለመውን የእድገት ዕቅዱን ለማሳካት እንደሚያግዘውም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2035 የአውሮፕላኖቹን ቁጥር ከ270 በላይ ለማድረስ ዕቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም