ቀጥታ፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  የህንድ ባለ ሀብቶች በክልሉ ኢንቨስት  እንዲያደርጉ  ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2016(ኢዜአ)፦የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ የህንድ  ባለ ሀብቶች በክልሉ ባሉ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንቨስት አንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከህንድ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ፌዴሬሽንና ኢንዱስትሪ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የንግድ ስብሰባ ላይ ርዕሰ መስተዳደሩ  ባደረጉት ንግግር የጋምቤላ ክልል  ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች አሉት።

በማብራሪያቸውም  ክልሉ በግብርናው ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች   ለም መሬትና የውሃ ሀብት መኖሩን አንስተዋል።

 አክለውም በክልሉ   በኢንዱስትሪ፣በማዕድን፣በቱሪዝም፣በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች  መዋዕለ-ነዋያቸውን  ለሚያፈሱ ባለ ሀብቶቹ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል።


 

በስብሰባው የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ፣የጋምቤላ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሎው ኡቡፕ አንዲሁም የመጀንግ ዞን አስታዳዳሪ ኤሊያስ ገዳሙ ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም፤ ከ30 በላይ የህንድ ኩባንያዎች መሳተፋቸውን በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም