ቀጥታ፡

አቶ መሳፍንት ተፈራ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2016(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ መሳፍንት ተፈራን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚነት ሹመትን አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ሹመቱን ያጸደቀው ዛሬ እያካሔደ ባለው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው።



 

በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ የአቶ መሳፍንት ተፈራን የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ ለምክር ቤቱ ካቀረቡ በኋላ በምክር ቤቱ አባላት ሐሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

የምክር ቤቱ አባላት የሰጡትን ሐሳብና አስተያየት ተከትሎም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም