ቀጥታ፡

አቶ ጌትነት ታደሰ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2016(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ጌትነት ታደሰን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ በማድረግ ሾመ።

ምክር ቤቱ ሹመቱን ያጸደቀው ዛሬ እያካሔደ ባለው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው።

በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ የአቶ ጌትነት ታደሰን የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ ለምክር ቤቱ ካቀረቡ በኋላ በምክር ቤቱ አባላት ሐሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።


 

የምክር ቤቱ አባላት የሰጡትን ሐሳብና አስተያየት ተከትሎም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

አቶ ጌትነት ታደሰ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

አቶ ጌትነት ታደሰ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም