የጃፓን ተመራማሪዎች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የእአምሮ እንቅስቃሴን የሚያሳይ የመጀመሪያውን ምስል ማግኘታቸው ተነገረ

395

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 8/2016 (ኢዜአ)፡- የጃፓን ተመራማሪዎች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሠው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሰው ልጅ አእምሮ የድርጊት እንቅስቃሴን የሚያሳይ የመጀመሪያውን ምስል መፍጠራቸው ተነገረ።

የጃፓን ብሔራዊ የኳንተም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲቲዩት እንዲሁም ሌሎች ተመራማሪዎች የሰው ልጅ አእምሮ ምስል ከሳች እንቅስቃሴ ላይ ባካሄዱት ጥናት አዲስ ውጤት ማግኘታቸው ተነግሯል።

ተመራማሪዎቹ ሠው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ባካሄዱት ጥናት በአእምሮ ውስጥ እንዴት ሙሉ ምስል ሊከሰት አንደሚችል የሚያሳዩ ቅድመ ሁኔታዎችን መገንዘባቸው የተመላከተ ሲሆን የአቦ ሸማኔ ሙሉ ገጽታን፣ የአውሮፕላንን ቅርጽንና የማብራት ምልክቶችን ግልጽ ምስል ማግኘታቸው ነው የተገለጸ።

በበዚኅም የሠው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የአእምሮ ምስል ከሳች እንቅስቃሴን በጉልህ የሚያሳይ የመጀመሪያውን ምስል ተመራማሪዎቹ ማግኘታቸውን ዥንዋ ዘግቧል።

"የአንጎል ዲኮዲንግ" የሚል ስያሜ በተሰጠው የቴክኖሎጂ ምርምር 1200 ምስሎች እና መሬት ላይ ያሉ ግዑዝ አካላት ከአእምሮ ጋር ያላቸው ግንኙነት የተጠና ሲሆን ምርምሩ በአእምሮ እንቅስቃሴ ላይ በመመስረት የሰው ልጅን የማስተዋል ይዘቶች ለማለየት እንደሚያስችል ተነግሯል።

የምርምሩ ግኝቶች በቅርቡ በሚታተመው ኢንተርናሽናል ሳይንቲፊክ ጆርናል ለእይታ እንደሚበቃም በመረጃው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም