የኢትዮ- ጃፓን የኢንቨስትመንት ፎረምና የፖለቲካ ምክክር በመጪው የካቲት በቶኪዮ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮ- ጃፓን የኢንቨስትመንት ፎረምና የፖለቲካ ምክክር በመጪው የካቲት በቶኪዮ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8/2016 (ኢዜአ) የኢትዮ- ጃፓን የኢንቨስትመንት ፎረምና የፖለቲካ ምክክር በመጪው የካቲት በቶኪዮ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሱጂ ኪዮቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል።
በፈረንጆቹ ከፊታችን የካቲት 26 እስከ 29 ቀን ድረስም የኢትዮ-ጃፓን የፖለቲካ ምክክር እንዲሁም የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በቶኪዮ ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን አምባሳደር ዳባ ተናግረዋል፡፡
ለፎረሙ ስኬታማነትም በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡፡፡
የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሱጂ ኪዮቶ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ልማት ጃፓን የምታደርገውን ተሳትፎ እና ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
በሁለቱ ሀገራት በቀጣይ ለሚካሄደው የፖለቲካ ምክክር በጃፓን በኩል አስፈላጊ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል።