ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን ያፀድቃል

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 8/2016 (ኢዜአ)፦ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ በ9ኛ መደበኛ ስብሰባው በቅድሚያ የ8ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን በማጽደቅ የዕለቱን ስብሰባ የሚጀምር ይሆናል፡፡

ጉባዔው በዕለቱ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢ ሹመትን መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሹመትን እንደሚያፀድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም