ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት ፓርቲዎች እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 8/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ እና ለዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ እውቅና መስጠቱን አስታወቀ።

ቦርዱ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ ሕጋዊ የክልል ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት መስጠቱን ገልጿል።

በተመሳሳይ ቦርዱ ለዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ ሕጋዊ የሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት መስጠቱን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም