ቀጥታ፡

4ኛው ዙር የኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 08/2016 (ኢዜአ)፦ 4ተኛው ዙር የኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የአሁኑ ድርድር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ተገናኝተው የሰጡትን የጋራ መግለጫ ተከትሎ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።


 

መሪዎቹ በውይይታቸው የሶስቱ ሀገራት ተወካዮች ድርድሩን በማፋጠን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት ቀጣይ ተግባራትን የተመለከቱ መመሪያዎች እና ደንቦችን እንዲያዘጋጁ ከመግባባት ደርሰው እንደነበር ከዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ እአአ በ2015 በወጣው የታላቁ ህዳሴ ግድብ መርሆች (declaration of principles) እንደምትመራና በምርህ ላይ ተመስርቶ ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ የአባይ ወንዝ አጠቃቀም ያላትን አቋም እንደምታጸና አምባሳደሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም