የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በጃፓኗ ካሳማ ከተማ ከተማ ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በጃፓኗ ካሳማ ከተማ ከተማ ተካሄደ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 7/2016 (ኢዜአ)፡- የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በጃፓን ኢባራኪ ግዛት ካሳማ ከተማ ተካሂዷል።
ማራቶኑ 18ኛው የካሳማ ከተማ የግማሽ ማራቶን ውድድር ሲሆን በውድድሩም ከ1600 በላይ ሯጮች መሳተፋቸውን በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በጃፓን የኢፌዲሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዳባ ደበሌ የግማሽ ማራቶን ውድድሩን አስጀምረዋል።
አምባሳደር ዳባ በዚሁ መሰል ውድድሮች ረጅም ዘመናት ያስቆጠረውን የሁለቱን አገራት መልካም ግንኙነት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር ሚናው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።
አምባሳደር ዳባ የጃፖን መንግስት ይህን ውድድር በማዘጋጀቱና የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።
የካሳማ ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ በበኩላቸው ከተማው ከኤምባሲው ጋር እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከንቲባው አክለውም ከከተማዋ አስተዳደር ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከከተሞች ጋር ጉድኝት በመመስረት በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።