ቀጥታ፡

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሠረተበትን 88ኛ በዓል በቢሾፍቱ ሐረር ሜዳ ግቢ አክብረናል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2016(ኢዜአ)፦ ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሠረተበትን 88ኛ በዓል በቢሾፍቱ ሐረር ሜዳ ግቢ አክብረናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

መሠረተ ልማትና ዘመናዊ ትጥቆችን ለማሟላት፤ ራስን በቴክኖሎጂ ለመቻል፣ ብቁና በቂ የሰው ኃይል ለማፍራት፤ የተደረገው ጥረት ሪፎርማችን ውጤታማ መሆኑን አሳይቷል ብለዋል።

በበዓሉ ላይ በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሁሉም ዘርፍ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና መምራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም