ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሠው አልባ የአየር ምድብን መርቀው ከፈቱ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሠው አልባ የአየር ምድብን መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2016(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሠው አልባ የአየር ምድብን መርቀው ከፍተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በከሠዓቱ መርሐ-ግብር የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን እጩ መኮንኖች፣ የአውሮፕላን ጥገና ሙያተኞችን እና ፓይለቶችን እንደሚያስመረቁ ይጠበቃል።
88ኛው የኢትዮጵያ አየር ሃይል የምስረታ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡