ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው በ3ኛ አመት ፤ 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር: አገልግሎት አሰጣጥ ፤ የሰው ኃይል እና የአሰራር ጥልቅ ሪፎርሞ መተግበሪያ ረቂቅ ደንብ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።

ውድ እና ውስን የሆነውን የከተማዋን መሬት ለማስተዳደር እና የከዚህ በፊት የአሰራር ችግሮችን በተደራጁ እና ብቁ በሆነ ሙያተኛ ሊያደራጁ የሚችሉ ፤ ዘመናዊ የአሰራር ዘዴን በሚያሳልጡ እና ብልሹ አሰራርን ሊከላከሉ የሚችሉ የህግ ማዕቀፎችን መርምሮ በማፅደቅ እና ትግበራው በጠንካራ ዲሲፕሊን እንዲመራ ውሳኔ አሳልፏል።

በሌላ በኩል የአብርሆት ቤተ መፅሀፍት እና የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነው የአድዋ ዐዐ ኪሎ ሜትር ሙዝየም ፕሮጀክት በአንድ የህግ ማዕቀፍ ማስተዳደር የሚቻልበትን ረቂቅ ደንብ መርምሮ በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም