ቀጥታ፡

"ጥቁር አንበሳ" የአየር ላይ ትርዒት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር ኃይልና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይል በጋራ "ጥቁር አንበሳ" የተሰኘ ልዩ የአየር ላይ ትርዒት እያካሄዱ ነው። 

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች  አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ኢብራሒም ናስር፣ ጄነራል መኮንኖች፣ የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል "በመስዋዕትነት ሀገርን የዋጀ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል" በሚል መሪ ኃሳብ ከሕዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል ማጠቃለያ መርኃ ግብር በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ እየተካሄደ ነው።

በአሁኑ ሰዓት የጥቁር አንበሳ የአየር ትርዒት እየተካሄደ ይገኛል።

የአየር ላይ ትርኢቱ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አየር ኃይል አባላት ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ጋር በመሆን ነው እያካሄዱት የሚገኙት።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም