የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦች እና ወታደራዊ አታሼዎች የአንድነት ፓርክን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦች እና ወታደራዊ አታሼዎች የአንድነት ፓርክን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 5/2016(ኢዜአ)፦ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦች እና ወታደራዊ አታሼዎች የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።
88ኛው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስረታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
በጉብኝቱ የበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦችና ወታደራዊ አታሼዎች እየተሳተፉ ነው።
የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦችና ወታደራዊ አታሼዎች በትላንናው ዕለት የኢትዮጵያ አየር ኃይልን የጎበኙ ሲሆን አየር ኃይሉ እያስመዘገባቸው ያሉ ለውጦችን፣ የደረሰበት ደረጃና በገነባው አቅም ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ተሳታፊዎቹ በዛሬው ዕለትም የአንድነት ፓርክና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።