የመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብን መርቀው ከፈቱ - ኢዜአ አማርኛ
የመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብን መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2016(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ቢሾፍቱ የሚገኘውን የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ መርቀው ከፍተዋል።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንንን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት የጦር መኮንኖችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ የባር፣ ሬስቶራንት፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የመኝታ ክፍል፣ መዋኛ ገንዳ፣ የቴንስ መጫወቻ እና ልዩ ልዩ የመዝናኛ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ በ1955 ዓ.ም የተገነባ ሲሆን ሙሉ እድሳት ተደርጎለት በዛሬው ዕለት ታህሳስ 05/2016 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።
ከምርቃቱ ቀጥሎም የምክክር መድረክ እና ጉብኝት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በትናንትናው ዕለትም የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ኃይል አዛዦች ሮረም በቢሾፍቱ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።