የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች ፎረም በስኬት ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች ፎረም በስኬት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 4/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አየር ኃይል አዘጋጅነት የተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች ፎረም ስኬታማ መሆኑን አየር ኃይሉ ገለጸ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል "በመስዋዕትነት ሀገርን የዋጀ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል" በሚል ከሕዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል።
ይህንንም ተከትሎ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች ፎረም በቢሾፍቱ ተካሂዷል።
በኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ኮሎኔል መሰረት ጌታቸው፤ ፎረሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በተካሄደው ፎረም ከ14 የአፍሪካ አገራት የተወጣጡ አዛዦችና ልዑካን እንዲሁም ከ12 ዓለም አቀፍ ተቋማት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች መገኘታቸውን ጠቁመዋል።
በፎረሙ የአፍሪካ አገራት አየር ኃይሎች ያለባቸውን ተግዳሮቶች በጋራ ሆነው መፍትሄ መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱንም ተናግረዋል።
የአፍሪካ አየር ኃይሎች ያለባቸውን ችግሮች በተናጠል ሳይሆን በጋራ መፍታት እንዳለባቸውም መጠቆሙን አንስተው ለዚህም የመፍትሄ ኃሳቦች ተመላክቷል ብለዋል።