ቀጥታ፡

በኢንቨስትመንት አማራጮች እና የገበያ ትስስሮች ዙሪያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ላሳዩ አምራች ኩባንያዎች ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 4/2016(ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፍ ላይ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሁም በዘርፉ የተፈጠሩ የገበያ ትስስሮች ዙሪያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ላሳዩ አምራች ኩባንያዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሶስተኛ ቀኑን በያዘው 27ተኛው የአለም የኢንቨስትመንት ኮንፍረንስ በኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲዎች መካከል በተደረገ የምክክር መድረክ የተጀመረ ሲሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡


 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በዚሁ መድረክ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በመድረኩም በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች እንዲሁም በዘርፉ የተፈጠሩ የገበያ ትስስሮች ዙሪያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ላሳዩ ተሳታፊ አምራች ኩባንያዎች ማብራሪያ መስጠታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም