ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ፓኪስታን በፀረ ሽብርና ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ዙሪያ ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ

አዲስ አበባ ፤ታህሳስ 04/2016(ኢዜአ):- በፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር አብዱላ ከፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳይ ጊዜያዊ ሚኒስትር ሳርፍራዝ ቡጉት ጋር የሁለቱን ሃገራት የግንኙነት መስክ ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

ኢትዮጵያና ፓኪስታን በሁለትዮሽ፣ ክልላዊ እና በባለብዙ ወገን ያላቸውን ትብብር በፀጥታ፣ በፀረ-ሽብርተኝነት እና ኢሚግሬሽን መሰኮች ማጠናከር እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።

አምባሳደር ጀማል በዚህ ወቅት እንዳሉት ሽብርተኝነትና ህገወጥ ንግድን ለመከላከለል በሃገራቱ መካከል የእውቀት ልውውጥ ለማድረግ ባለሙያዎች ተቀራርበው መስራት የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር ይገባል።


 

የፓኪስታን አገር ውስጥ ጉዳይ ጊዜያዊ ሚኒስትር ሳርፍራዝ ቡጉት በኢትዮጵያ እየመጣ ያለውን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት አድንቀው ፣ ፓኪስታን ከአፍሪካ ጋር ላላት ግንኙነት ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና የምትጫወት ሃገር መሆኗን ተናግረዋል።

በተጠቀሱት መስኮች የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት መጠናከር የሃገራቸው ፍላጎት ስለመሆኑ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም