ቀጥታ፡

የፓስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት ሥራን በኢትዮጵያ መጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፤ ታኅሣስ 3/2016 (ኢዜአ) ፦ የፓስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት ሥራን በኢትዮጵያ መጀመር የሚያስችል ስምምነት በተለያዩ ተቋማት መካከል ተፈርሟል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት የተሻሻሉ የደኅንነት ባሕሪያትን በማምጣት በኩል ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑም ተመላክቷል።

የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት እና ቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር የፓስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት ሥራን በኢትዮጵያ መጀመር የሚያስችላቸውን ሥምምነት ነው የተፈራረሙት።

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ የፓስፖርት ቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑንም ነው ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተገኘው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

ሥምምነቱ የኢትዮጵያን የፓስፖርት አሠራር በማዘመን፣ አዲስ ለተነደፈው የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት የተሻሻሉ የደኅንነት ባሕሪያትን እና የተሻሻለ ቅልጥፍናን በማምጣት በኩል ትልቅ ጥቅም አለውም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ለኢትዮጵያ የፓስፖርት ቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን የሚያመላክት እንደሆነም ነው የተመላከተው፡፡

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ወደ ተሻለ የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት እንከን የለሽ ሽግግር ለማድረግ ቃል መገባቱም ተጠቅሷል፡፡

የፓስፖርት ማተሚያ ፋብሪካው በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ እንደሚሆንም ተጠቅሷል፡፡

ሥምምነቱ በማንነት፣ በሰላማዊ ጉዞ እና በደኅንነት ዙሪያ ትልቅ ጥቅም እንዳለውም በመረጃው ተጠቁሟል።

ስምምነቱን የፈረሙት የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት፣ ቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እና የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም