ቀጥታ፡

የኢትዮጵያን የግብርና ምርቶች የሚያስተዋውቅ መካነ ርዕይ በኳታር ዶሃ ተከፈተ

አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 3/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የግብርና ምርቶች የሚያስተዋውቅ መካነ ርዕይ በኳታር ዶሃ ተከፍቷል።

መካነ ርዕዩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የኢትዮጵያን የግብርና ምርቶች የሚያስተዋውቀውን መካነ ርዕይ መርቀው ከፍተዋል።

መካነ ርዕዩ ይፋ የተደረገው በኳታር እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአትክልት እና ፍራፍሬ አውደ ርዕይ ላይ ነው።


 

በመርኃ-ግብሩ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሶፊያ ካሳ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ፣ የኢትዮጵያ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች ማህበር ሰብሳቢ ነጋ መኳንንት፣ አምባሳደሮች፣ የኳታርና የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ በዶሃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም