የጂቡቲ የቢዝነስ ልዑክ በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ቦታዎችን ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
የጂቡቲ የቢዝነስ ልዑክ በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ቦታዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 03/2016 (ኢዜአ)፦ የኦስትሪያ እና የጁቡቲ ኩባንያዎች በመጣመር በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማየት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ስፍራዎችን ጎብኝቷል።
የቢዝነስ ልዑኩ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
ልዑኩ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ስፍራዎችን መጎብኘቱን በጁቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
የቢዝነስ ልዑኩ ባለፈው ሳምንት በኤምባሲው ተገኝቶ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች በተመለከተ በጁቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጋር በስፋት መወያየታቸውም ተጠቅሷል።