በአቧራ ማጽጃ ማሽን ውስጥ የተገኘው የአልማዝ ቀለበት

398

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 03/2016(ኢዜአ)፦ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ግምት ያለው የአልማዝ ቀለበት ከ48 ሰዓት ፍለጋ በኋላ በአቧራ ማጽጃ ማሽን ውስጥ መገኘቱ ተሰምቷል።

በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ የሚገኘው ዘ ሪትዝ ቅንጡ ሆቴል ደንበኛ የሆነችው ማሌዢያዊት ባለሃብት ለፓሪስ ፖሊስ የንብረት ጠፍቶኛል ሪፖርት ተቃርባለች።

የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ገበያ በወጣሁበት ወቅት የአልማዝ ቀለበቴ ጠፍቷል ለዚህም የሆቴሉ ሰራኞች ይመርመሩልኝ ስትል ነው ለፖሊስ ሪፖርት ያቀረበችው።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በመለየት በሆቴሉ ሰራተኞችና የጥበቃ ክፍል አበላት የአልማዝ ቀለበቱ ፍለጋ የተከናወነ ሲሆን በክፍል አቧራ ማጽጃ ማሽን(ቫኪዉም) ውስጥ ቀለበቱ እንደተገኘ ዩፒአይ ዘግቧል።

የሆቴሉ የጽዳት ሰራተኞች ክፍሉን በሚያጸዱበት ጊዜ ማሽኑ በሚያወጣው ነፋስ ቀለበቱ ሊሳብና ውስጡ ሊገባ እንደቻለ ነው የተገለጸው።

ቅዳሜለት የጠፋውን ቀለበት በለንድን የምትገኘው ባለንብረት ወደ ፓሪስ መጥታ መውሰድ እንደምትችልም ፖሊስ ገልጿል።

ዘ ሪትዝ ሆቴል በፓሪስ ከሚገኙ ቅንጡ ሆቴሎች መካከል አንዱ ሲሆን ለአንድ ምሽት ቆይታ ከ2 ሺህ እስከ 50 ሺህ ዶላር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚጠይቅ በመረጃው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም