ከ3 ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ውደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል - ኢዜአ አማርኛ
ከ3 ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ውደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2016(ኢዜአ)፦ ከ3 ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ውደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ።
ለ2016/17 የምርት ዘመን ከውጭ ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 610 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ተጨማሪ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጂቡቲ ወደብ መድረሷን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል።
የማዳበሪያውን መምጣት ተከትሎ እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሰባት ዙሮች ከውጭ የተጓጓዘው የማዳበሪያ መጠን ወደ 3 ሚሊዮን 310 ሺህ ኩንታል ከፍ ብሏል።
ከዚህ ውስጥ እስከአሁን 2 ሚሊዮን 40 ሺህ 479 ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ለአርሶ አደር ዩኒየኖች በመሰራጨት ላይ መሆኑን ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።
በመጪው ታህሳስ 4 ቀን 520 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ እንዲሁም ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም 390 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን እና 160 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ማዳበሪያ የጫኑ ሁለት መርከቦች ወደብ እንደሚደርሱም ይጠበቃል።