የኢትዮጵያና ኳታር መልካም የፖለቲካ ግንኙነትን ህዝቦችን ተጠቃሚ ወደሚያደርግ የኢኮኖሚ አጋርነት መቀየር ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያና ኳታር መልካም የፖለቲካ ግንኙነትን ህዝቦችን ተጠቃሚ ወደሚያደርግ የኢኮኖሚ አጋርነት መቀየር ይገባል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2016(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ኳታር መካከል ያለውን መልካም የፖለቲካ ግንኙነት ህዝቦችን ተጠቃሚ ወደሚያደርግ የኢኮኖሚ አጋርነት መቀየር አስፈላጊ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለፁ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዶሃ ፎረም ጎን ለጎን ከኳታር የልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ከሊፋ ቢን ጃሲም አል ኩዋሪ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይታቸው ረዥም ዘመን ባስቆጠረው የኢትዮጵያ እና የኳታር የልማት ፈንድ ትብብር ዙርያ ያተኮረ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ኳታር በኢኮኖሚያዊ ትብብር መስክ ተመራጭ መሆኗን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን መልካም የፖለቲካ ግንኙነት ህዝቦችን ተጠቃሚ ወደሚያደርግ የኢኮኖሚ አጋርነት መቀየር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያን እና የኳታር ልማት ፈንዱ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማስፋትና ከፍ ማድረግ ለግንኙነቱ እድገት አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡